አፈንዲ ሙተቂ በጅቡቲ ሪፐብሊክ sound effects free download

By afendi1978

0 Downloads

15 hours ago

0 seconds

afendi1978 Sound Effects

About አፈንዲ ሙተቂ ----- በጅቡቲ ሪፐብሊክ Mp3 Sound Effect

አፈንዲ ሙተቂ ----- በጅቡቲ ሪፐብሊክ በ1985 የተነሳ ፎቶግራፍ ነው። በስተቀኝ በኩል ያለው ማን እንደሆነ አልታወቀም። በስተግራ በኩል ጊታር ይዞ "ኮራ፣ ቀብረር" ብሎ የተቀመጠው ግን በጣም የምንወደው የድሬ ዳዋ ቀሽቲ ነው። ከማንም በላይ የዓሊ ቢራ የቅርብ ጓደኛ የነበረው ይህ አርቲስት ነው። አወቃችሁት? እስቲ ዘፈኑን ልጠቀስላችሁ። "ሲሲ ሲቱ ቲያ አስጎሪ ጎሪ ኮቱ ገማ ኪያ ቦጂቴ ኦኔ ቲያ ቦቺፍቴ ኢጃ ቲያ" ---- "ሲሲ" እጅግ በጣም ከሚወደዱት የአፋን ኦሮሞ ዘፈኖች መካከል አንዱ ነው። ዓሊ ቢራ፣ መሐመድ ጠዊል፣ ያሕያ አደም እና ሌሎችም ዘፍነውታል። ኦሪጅናሌው ዘፋኝ ግን በፎቶግራፉ ላይ የምትመለከቱት ምርጥ አርቲስት ነው። ኢብራሂም ዩሱፍ ይባላል። ብዙዎች የሚያውቁት ግን "ሂሜ" በተሰኘው ቅጽል ስሙ ነው። ሂሜ ዩሱፍ የሰሩትን ያህል ካልተነገረላቸው ድንቅ አርቲስቶች አንዱ ነው። "Yaa Hurree Faana Roobaa", " Biyyoo Adaree" "Fayfayoo Haramayaa" የሚባሉትን ተወዳጅ ዘፈኖች የተጫወተው እርሱ ነው። --- ሂሜ ዩሱፍን "ኡመተ ፈናን ቀሽቲ ድሬ ዳዋ" በተሰኘው መጽሐፌ ውስጥ ዘክሬዋለሁ። በቅርቡ ባሳተምኩት "ቦረና እና በሬንቱ'" የተሰኘ መጽሐፍ ውስጥም በጥቂቱ አውስቼዋለሁ። ነገር ግን ለሂሜ በቂ አይደለም። ወደፊት ስለህይወቱ እና ስለስራዎቹ በሰፊው እናወጋለን። ---- አፈንዲ ሙተቂ ነሐሴ 24/2017
አፈንዲ ሙተቂ በጅቡቲ ሪፐብሊክ Sound Effects Free Download. Sound Effects Downloader To Help You Download The Highest Quality አፈንዲ ሙተቂ በጅቡቲ ሪፐብሊክ Sound Effects Free Download For TikTok Videos. You Just Search Sound Effects And Download.

My You Like It