Afendi Muteki አቲካ ኒብራስ sound effects free download

By afendi1978

0 Downloads

4 days ago

0 seconds

afendi1978 Sound Effects

About Afendi Muteki ---- አቲካ ኒብራስ Mp3 Sound Effect

Afendi Muteki ---- አቲካ ኒብራስ በአንድ በኩል የጓደኞቼ የነ አንዋር ኒብራስ እህት ናት። በሌላ በኩል የካራ-ቁርቁራው ጓደኛዬና ወዳጄ የአቶ ኒብራስ ጀውሃር ልጅ ናት። ከትናንት ወዲያ ማታ በዚህ ወቅት ጽፌው እያጠናቀቅኩት ባለው መጽሐፍ የአቶ ኒብራስን የወጣትነት ፎቶ ለማስገባት ፈለግኩኝና ወደ ኢንቦክሷ ሄጄ እንዲህ አልኳት። "የአባትሽ አንድ የቆየ ፎቶግራፍ ካለሽ በኢንቦክስ ላኪልኝ። በመጽሐፌ ውስጥ ላካትተው ነው። ከአባትሽ ጋር የገለምሶ፣ የበዴሳ፣ የመቻራ፣ የዋጩ፣ የድሬዳዋ ሰዎችም ታሪካቸው ተጽፏል። ፎቶአቸውም አለ። ስለዚህ የእርሱን ፎቶ ፈጠን ብለሽ ላኪልኝ" አቲካ መልስ ስትሰጠኝ "ጥሩ ነው ያሰብከው። ሆኖም የቤተሰባችንን ፎቶዎች የሚሰበስበው ሰው ለዘልዓለሙ ስለሄደ እኔ ልሰጥህ አልችልም" አለችኝ። አባባሏ ግራ የሚያጋባ ነው። "ምን ማለቷ ነው? የአባቴ ፎቶ አይግባ ነው?" ብዬ አጠነጠንኩ። አቲካ ቀልደኛም ስለሆነች እንደ ሌላ ጊዜ የምትቀልድ መሰሎኝ ነበር። እናም "ማን ነው የቤተሰባችሁን ፎቶ የሚሰበስበው። ደግሞም ለዘልዓለሙ ሄዷል ምን ማለት ነው? ሰውዬው ሞቷል ማለትሽ ነው" አልኳት። መልስ አልሰጠችኝም። ትናንት ነው ነገሩ የገባኝ። ብዙ የአካባቢያችን ሰዎች "ገና እምቡጥ አበባ የሆነችው ተሚማ ኒብራስ በሀገረ ኖርዌይ በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደለች" እያሉ የጻፏቸውን ፖስቶች ሳይ ብዙ ስሜቶች በደም ስሬ ተሰራጩ። የማውቀው ሰው ይቅርና የማላውቀው ሰው "ተገደለ" ሲሉኝ እንኳ በሐዘን፣ በንዴትና በቁጭት መካከል እወራጫለሁ። ትናንት ግን የማውቃት፣ የአመለ-ሸጋው ጓደኛዬ እና ወዳጄ የአቶ ኒብራስ ልጅ ተገደለች ነው ያሉኝ። ------ አዎን! ታዳጊ ሴት፣ ሃያ ዓመት ያላለፋት ቡቃያ፣ በትምህርት በጣም ጎበዝ፣ የሀረር ልጅ፣ የኦሮሚያ ልጅ፣ የኢትዮጵያ ልጅ፣ የአፍሪቃ ልጅ ጥቁሮችንና ሙስሊሞችን እጅግ በሚጠላ አንድ supermacist ቅዥቢ ፈረንጅ ተገድላለች። ------ ኖርዌይ፣ መላው አውሮጳ እና አሜሪካ በአንድ ጎናቸው ለሰብዓዊነት እየተቆረቆሩ በሚፈጽሟቸው ተግባራት ደስ ይላሉ። በድቡቁ ጎናቸው ግን ሀገራቱም ሆነ መንግሥታቱ ለጥቁር፣ ለአፍሪቃዊ፣ ለሙስሊም፣ ለሩሲያዊ ለዐረብ፣ ለህንድ፣ ለቻይናዊ እና ለእስያዊ መጥፎ አመለካከት ነው ያላቸው። ይህንን በመንግሥት ደረጃ ለመገንዘብ ካስፈለገ እስራኤል በጋዛ ህዝብ ላይ የምትፈጽመውን የዘር ማጥፋት ዘመቻ በመሳሪያ እና በገንዘብ የሚደጉሙበትን ሁኔታ መመልከት ይቻላል (ጄኖሳይድ ፈጻሚዋን ለመቅጣት ከታሰበ አሜሪካ vetto power ትጠቀማለች። በሞራል፣ በመሳሪያ እና በፋይናንስም እስራኤልን ትረዳለች)። በግለሰብ ደረጃ ደግሞ ከትራምፕ ጀምሮ፣ ቀኝ አክራሪዎች፣ የናዚ ናፋቂዎች፣ አክራሪ ክርስቲያኖች፣ እና የነጭ የበላይነት አቀንቃኞች የሚነዙትን ፕሮፓጋንዳ፣ የሚያስፋፉትን የጥላቻ ዘመቻ እና የሚፈጽሟቸውን በርካታ ግድያዎች ማየት በቂ ነው። በእርግጥ በየሀገራቱ ያለው ሕዝብ በአብዛኛው ሰላማዊ ነው። ከሀገራቱ ሕዝቦች መካከል ለአፍሪቃ፣ ለኢትዮጵያ፣ ለሙስሊሞችና ለፍልጥኤማዊያን የሚቆረቆሩ ብዙ ነጮች አሉ። ይሁንና የነጭ የበላይነት ሰባኪዎቹና አማኞቹ ሀይልና ገንዘብ ስላላቸው ተራው ሕዝብ ሊያስቆማቸው አልቻለም። የሚሰሩት ወንጀልም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው የሄደው። ------ ተሚማን የበላው ጅብ በነዚህ የነጭ የበላይነት አስተርዮ የተጠመቀ መሆኑን የኖርዌይ መንግሥት ገልጿል። ገዳዩም በቁጥጥር ስር ውሏል። ነገር ግን ልጃችን ትክክለኛ ፍትሕ ታገኝ ዘንድ አስፈላጊው ሥራ ሁሉ መሠራት አለበት። በዚህ ረገድ በኖርዌይ የሚኖሩት የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት፣ የኦሮሞ ማህበረሰብ አባላት፣ የሙስሊም ማህበረሰብ አባላት፣ በዜግነታቸው ኖርዌጂያን የሆኑ የኢትዮጵያ ወደጆች ( ለምሳሌ Terje Østebø , Kjetil Tronvoll, ወዘተ)፣ በኖርዌይ የሚኖሩት እንደ ጋሼ አበራ ለማ ( Abera Lemma እና Mohamed Kheir Omer ) ዓይነት ተጽእኖ ፈጣሪ ግለሰቦችና ሌሎችም የሚጠበቅባቸውን ሁሉ ያደርጉ ዘንድ በፈጣሪ ስም እንጠይቃለን። ሌላው ደግሞ ሴት ልጆችን ማርሻል አርት ማስተማርን ባህላችን ብናደርግ ጥሩ ይመስለኛል (በዚህ ርእስ ላይ ሌላ ጊዜ እንወያያለን! ኢንሻ አላህ)። -------- በጣም ነው ያዘንኩት። ለወጣት ተሚማ አላህ ጀንነትን ይስጣት። ከሸሂዶች ውስጥ ይመዝግባት። ለአቶ ኒብራስ ቤተሰብ፣ ለዘመድ አዝማድ፣ ለወዳጆችና ተሚማን ለሚያውቋት ሁላ ሰብርና መጽናናትን ይስጣቸው። ኣሚን። ኣሚን! አላሁመ ኣሚን! ------ አፈንዲ ሙተቂ ነሐሴ 20/2017
Afendi Muteki አቲካ ኒብራስ Sound Effects Free Download. Sound Effects Downloader To Help You Download The Highest Quality Afendi Muteki አቲካ ኒብራስ Sound Effects Free Download For TikTok Videos. You Just Search Sound Effects And Download.

My You Like It