About አፈንዲ ሙተቂ ---- ኢትኖግራፈር ባለቤትነቱ Mp3 Sound Effect
አፈንዲ ሙተቂ ---- ኢትኖግራፈር ባለቤትነቱ የሁሉም ህዝቦች ነው፡፡ ሁሉንም ህዝቦች ያገለግላል፡፡ ሁሉንም ቋንቋ እንደራሱ ቋንቋ ይመለከታል፡፡ ብዙ ቋንቋ ለመናገርና ለመጻፍ ይጥራል፡፡ በሙያውና በአምሮቱ ደግሞ ለኪነ-ጥበብ እጅግ በጣም ቅርብ ነው፡፡ እኛም በዚሁ መንፈስ እየተነዳን ነው በተለያዩ ቋንቋዎች የተዘፈኑ ዜማዎችን እየሰማን ስሜታችንንና ትዝብታችንን ስንገልጽ የኖርነው፡፡ በዛሬዋ ሌሊትም "እስቲ ትንሽ ዘና ልበል" አልኩና Youtube የተሰኘውን ዓለም አቀፍ የቪዲዎች ድረ-ገጽ ከፈትኩ፡፡ በዋናው ገጽ (home page) መጀመሪያ ላይ ከመጡልኝ ቪዲዮዎች መካከል አንዱ ልጅነታችንን ያሳመረልን ተወዳጁ ድምጻዊ ኬኔዲ መንገሻ የተጫወተው “እንዲያው የሆዴን” የተባለው ዝነኛ ዘፈን ነው፡፡ እኔም ዘፈኑን አጣጣምኩትና ትዝታዬን ቀስቅሼ ሰገርኩበት፡፡ እስቲ ከግጥሙ ትንሽ ቆንጠር እናድርግ፡፡ ---- እንዲያው እንዲያው እንዲያው የሆዴን (2) እንዲያው እንዲያው እንዲያው የሆዴን (2) ---- በምሽት ጨረቃ በንጋት ፀሐይ አብረን ያሳለፍነው ይረሳሻል ወይ ደርሶ መሸት ሲል ክፉ አመል ይዞኛል እንደ አመለኛ ልጅ ግልፍ ያደርገኛል፡፡ (ያደርገኛል… አቤት… ያደርገኛል.. አሃ) --- አዝማች--- ከነ ሠራዊቱ ትዝታ ዘምቶበት ሳስቶ ቀረ አንጀቴ ሌላ እንዳይገባበት እርሳ ካለኝ ልርሳ ከእርሷ ምን ያምረኛል አመሏ እየከፋ እራቅ ያደርገኛል፡፡ (ያደርገኛል… አቤት… ያደርገኛል.. አሃ)…. ---- ሙሉውን ዘፈን ለመስማት ተከታዩን ሊንክ ይክፈቱ፡፡ https://www.youtube.com/watch?v=E5Jp9LaqhOw&list=RDMME5Jp9LaqhOw&start_radio=1 ---- እዚህ ላይ ብዙ ማለት ቢቻልም ሁለት ነገሮች ሳይጠቀሱ የሚታለፉ አይደሉም፡፡ የግጥሙ አጨራረስ እና እና የሙዚቃ ቅንብሩ፡፡ ከአዝማቹ ቀጥሎ ያሉት ባለ አራት መስመር ግጥሞች በሙሉ የሚያሳርጉት “ያደርገኛል” በሚል ቃል ነው፡፡ ይህም ግጥሙ lyric ብቻ ሳይሆን rhythmic መሆኑን የሚያሳይ አብነት ነው፡፡ ገጣሚው ከግጥሙ መልእክት በላይ ለግጥሙ ውበት መጨነቁ የሚያስታውቀው ግጥሞቹን እንዲህ rhythmical እንዲሆኑ አድርጎ በማሰናኘቱ ነው፡፡ ይህ ባሕሪ በተለይም በዐረብኛ እና በፋርስ ግጥሞች ላይ የሚታይ ነው፡፡ ዘፈኑን በሙዚቃ ያጀበው ዝነኛው ሮሃ ባንድ ነው፡፡ የሮሃ ባንድ ሙዚቀኞች ሙዚቃ ሲጫወቱ ሥራቸው ጥዑም ከመሆኑ ባሻገር እያንዳንዱ የሙዚቃ መሣሪያ ሳይታፈን በቀላሉ ጎላ ብሎ ይሰማል፡፡ በዚህም ዘፈን ውስጥ የዳዊት ይፍሩ ኦርጋን፣ የኤሊያስ በቀለ ድራም፣ የጆቫኒ ሪኮ ቤዝ ጊታር፣ የሰላም ስዩም ሊድ ጊታር፣ የያሬድ ተፈራ አልቶ-ሳክስፎን እና የፈቃደ ዐምደ መስቀል ቴነር-ሳክስፎን በደንብ ይሰማሉ፡፡ ----- ኬኔዲ መንገሻ በድንገት ብቅ ብለው ላይመለሱ ከጠፉብን ከዋክብት አንዱ ነው፡፡ ይህ አርቲስት በ1985 መጨረሻ ላይ ሲያርፍ ገና የ29 ዓመት ወጣት ነበር፡፡ ኬኒዲ በመጀመሪያ ካሴታቸው በሙዚቃ ኢንዱስትሪው ላይ መንገሥ ከቻሉ ጥቂት አርቲስቶችም አንዱ ነበር፡፡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ሰርተው ካለፉት አርቲስቶች መካከልም የሚመደብ ነው፡፡ ብዙዎች “መልከ-መልካም ነው” እያሉ ይገልጹት የነበረው ትዝተኛው ኬኔዲ መንገሻ ከ1979-1985 በነበሩት ዓመታት “በመላ ነው” (1979)፣ “እንዲያው የሆዴ” (1980)፣ “ቀፎኛል” (1982)፣ “ልሁን ደህና” (1984) እና “እምባ ስንቅ አይሆነኝ” (1985) የተሰኙ አልበሞችን ሰርቷል፡፡ በ1981 ከአሰፉ ደባልቄ፣ ከራሄል ዮሐንስ እና ከተሾመ አሰገድ ጋር፣ 1982 ከየሺመቤት ዱባለ ጋር እንዲሁም በ1983 ከብርቱካን ዱባለ ጋር በህብረት በሠራቸው ስራዎችም በርካታ ተወዳጅ ዜማዎችን ተጫውቷል፡፡ ይህ ተወዳጅ አርቲስት የተወለደው በአዲስ አበባ ከተማ፣ ተክለ ሃይማኖት አካባቢ ሲሆን ሲሞት የተቀበረውም በተክለ ሃይማኖት ቤተ ክርስቲያን ነው፡፡ ኬኔዲ ከአርቲስትነቱ ባሻገር በቀናነቱና በመልካምነቱ የሚወሳ ነው፡፡ RIP Kennedy the great! ---- አፈንዲ ሙተቂ ታሕሳስ 24/2013 © Afendi Muteki, July 18/2023 ----- ትክክለኛዎቹ የሶሻል ሚዲያ አድራሻዎቼ የሚከተሉት ናቸው። = የፌስቡክ ፔጅ (My New Facebook Page) https://www.facebook.com/AfendiEthno2018 => የቴሌግራም ቻነል (My Telegram Channel) https://t.me/afandishaHararአፈንዲ ሙተቂ ኢትኖግራፈር ባለቤትነቱ Sound Effects Free Download. Sound Effects Downloader To Help You Download The Highest Quality አፈንዲ ሙተቂ ኢትኖግራፈር ባለቤትነቱ Sound Effects Free Download For TikTok Videos. You Just Search Sound Effects And Download.