አፈንዲ ሙተቂ እስቲ ዛሬ sound effects free download

By afendi1978

0 Downloads

3 days ago

0 seconds

afendi1978 Sound Effects

About አፈንዲ ሙተቂ -------- እስቲ ዛሬ Mp3 Sound Effect

አፈንዲ ሙተቂ -------- እስቲ ዛሬ በኮምጣጣ እና ጎምዛዛ ወግ ወጥተን በመሪዎቻችን ዙሪያ ስለተነገሩ ቀልዶች እናውጋ። ------------ ግርማዊ ጃንሆይ የአማኑኤል ሆስፒታልን ሊጎበኙ ሄዱ፡፡ አንዱ ሻል ያለው እብድ እንዳያቸው ተጠጋቸውና “አንተ ማን ትባላለህ?” አላቸው፡፡ “ሞአ አንበሳ ዘእም ነገደ ይሁዳ ስዩመ እግዚአብሄር ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሤ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ነን” አሉት ጃንሆይ፡፡ ይህንን የሰማው እብድ ሳቅ እያለ “ጉድ ነው! እኔንም እብደት ሲጀምረኝ እንዲህ ነበር ያደረገኝ” አላቸው፡፡ (በርሱ ቤት ጃንሆይ ሊታከም የመጣ እብድ መስሎታል) ------------ ጃንሆይ እና ጸሓፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ከተማ ወርደው መዝናናት አማራቸውና ተያይዘው ወጡ። የተቻለውን ያህል ጥንቃቄ እያደረጉ ሲዝናኑ ከቆዩ በኋላ መሸ። በፒያሳ በኩል ወደ ቤተ መንግሥት በመመለስ ላይ ሳሉ ሲኒማ ኢትዮጵያ ደረሱ። “እስቲ እዚህም ገብተን ትንሽ እንይ” አሉና ወደ ሲኒማው ገብተው ከተመልካቾች ተርታ ተቀመጡ። በዚያ ዘመን ቴሌቭዥን በየቤቱ ስለሌለ ህዝቡ ወደ ሲኒማ ሄዶ ነው ዜና የሚከታተለው። በዜና ላይ ጃንሆይ የታዩ እንደሆነ ደግሞ ማጨብጨብ የዘመኑ ደንብ ነው። ታዲያ ዜና አንባቢው “ግርማዊ ጃንሆይ ዛሬ የጃፓን አምባሳደርን የሹመት ደብዳቤ ተቀበሉ” አለና ዜናውን በምስል አቀረበው። ይሄኔ በአዳራሹ የነበረው ጠቅላላ ህዝብ አጨበጨበ። አሁንም ሌላ የጃንሆይ ዜና ቀረበ። ህዝቡም አጨበጨበ። ሌላ የጃንሆይ ዜና ተከተለ። ህዝቡ አፍታ በአፍታ ማጨብጨቡን ቀጠለ። ጃንሆይና ጸሐፌ ትዕዛዝ ግን አላጨበጨቡም። ይህንን ያየ አንድ ጎልማሳ ተመልካች ወደ ጃንሆይ ተጠግቶ “ሽሜ! ጉድ ሳይፈላብሽ ብታጨበጭቢ ይሻልሻል” አላቸው። --------- ጓድ ሊቀመንበር መንግሥቱ ኃይለማሪያም የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በጠራው ስብሰባ ለመካፈል ጄኔቭ ሄዱ፡፡ ስብሰባው ከመጀመሩ በፊት ግን የእያንዳንዱ መሪ አመለካከት መታወቅ እንዳለበት ተወሰነ፡፡ መሪዎቹም እንደ ኪሎ መመዘኛ ሚዛን ካለ ማሽን ላይ እየወጡ አቋማቸውን ያስመረምሩ ጀመር፡፡ በመጀመሪያ የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጂሚ ካርተር ከማሽኑ ላይ ወጡ፡፡ ማሽኑ “Imperialist” ብሎ ጻፈ፡፡ ቀጥሎም የሶቪየት ህብረቱ ጓድ ሊዮኒድ ብሬዥኔቭ ከማሽኑ ላይ ወጡ፡፡ ማሽኑም “Socio- Imperialist” ብሎ ጻፈ፡፡ ሊቀመንበር መንግሥቱ ይህንን ሲያዩ ደነገጡ፡፡ “ጓድ ብሬዥኔቭን የመሰሉ ታላቅ መሪ እንዲህ ብሎ የገለጸው ማሽን እኔንስ ምን ይለኝ ይሆን?” እያሉ ተጨነቁ፡፡ እናም በፍራቻ አንድ እግራቸውን ከማሽኑ ላይ አስቀመጡ፡፡ ማሽኑ “Co” ብሎ ጻፈ፡፡ መንጌ “Communist ሊለኝ ነው” በማለት ደስ እያላቸው ሁለተኛውን እግራቸውን ሲያቀምጡ ማሽኑ “Confused” ብሎአቸው እርፍ! ------ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ አንድ ሚኒስትራቸው ታሞ ሊጠይቁት ሄዱ፡፡ ሰውዬውን “ምን ሆንክ” ቢሉት “እባጭ ወጥቶብኝ እንዲህ አቆሰለኝ” አላቸውና ቁስሉን አሳያቸው፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ “ይህቺው ናት ያሳመመችህ? አይዞን አሁን አደርቃታለሁ” አሉና ቁስሉን ያዙት፡፡ ከዚያም “አብዮታዊ ዲሞክራሲ! አብዮታዊ ዲሞክራሲ! አብዮታዊ ዲሞክራሲ” እያሉ መደጋገም ጀመሩ፡፡ ባለስልጣኑ ተገርሞ “እንዴ! አብዮታዊ ዲሞክራሲ ቁስል ያደርቃል እንዴ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር” ቢላቸው “በአብዮታዊ ዲሞክራሲ እንኳን ይህችን ቁስል ትልቋን ኢትዮጵያን አድርቀናታል” በማለት መለሱለት ይባላል። ------- ኢትዮጵያ እና ኤርትራ በ1990 ከተጣሉ በኋላ ነበር አሉ። መሪዎቹ የቡርኪናፋሶ ዋና ከተማ በሆነችው ዋጋዱጉ ያደረጉት የሰላም ንግግር ከከሸፈ በኋላ መለስ ዜናዊ ወደ ሀገር ውስጥ ገቡ። ከዚያም ለጋዜጠኞች መግለጫ ሲሰጡ እንዲህ አሉ። "ከእንግዲህ ለሻዕቢያ በሚገባው ቋንቋ እንነግረዋለን" ታዲያ ምሽት ላይ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ ከአስመራ ደወሉላቸው እና ሳቅ እየቀደማቸው እንዲህ አሏቸው። "ቂቂቂቂቂቂቂ...ሃሃሃሃ... ቀን ምን ነበር ያልከው ባክህ? በሚገባው ቋንቋ ስትል ትግርኛ ማለትህ ነው? ሻዕቢያ ትግርኛ ብቻ ሳይሆን አማርኛም ይሰማል። እስቲ በአማርኛ ንገረን ጓድ!" -------- አፈንዲ ሙተቂ መጀመሪያ መስከረም 2006 ተለጠፈ። ከአስር ዓመት በኋላ መስከረም 6/2016 በድጋሚ ተለጠፈ። ©Afendi Muteki, September 2023 ----- የቴሌግራም ቻናሌ የሚከተለው ነው። You may join my telegram channel here https://t.me/afandishaይባላል።
አፈንዲ ሙተቂ እስቲ ዛሬ Sound Effects Free Download. Sound Effects Downloader To Help You Download The Highest Quality አፈንዲ ሙተቂ እስቲ ዛሬ Sound Effects Free Download For TikTok Videos. You Just Search Sound Effects And Download.

My You Like It