ሙሉቀን መለሰ🥺💔 ''ምነው ከረፈደ'' sound effects free download

By musictube369

1795 Downloads

1 weeks ago

488 seconds

musictube369 Sound Effects

About ሙሉቀን መለሰ🥺💔 ''ምነው ከረፈደ'' Mp3 Sound Effect

ሙሉቀን መለሰ🥺💔 ''ምነው ከረፈደ'' መኪናን በዝግታ እያሽከረከሩ ለማድመጥ ምርጥ የሆነ ሙዚቃ እኮ ነው። 😏አዎ! መኪና የለኝም ግን ዋናው ቁምነገር እሱ አይደለም 😑 እኔ የምለው it's too late to say sorry! ኩረጃ መሆኑ ነው?🤧😂 -እስቲ ወደ ቁም ነገሩ እንመለስና በጣም እየናፈቀኝ ሙዚቃውን ደጋግሜ አደምጠዋለሁ። በተለይ "ምነው ከረፈደ" የሚለውን ... አላውቅም ብቻ የዚህ ሰው ውለታ አለብን ...🙌🥺 "በሚስጥር ቅበሪኝ" ን ሰምታችሁታል ግን ? ... "ዓይኔማ ወዳጅሽ" ንስ ... "እኔስ ተሳስቼ ወድጄሽ ነበረ " .... የሙሌ ሙዚቃዎች በድን አካልን መቀስቀስ የሚችሉ ፣ የጠወለገች ነፍስን የሚያለመልሙ ናቸው እኮ💙። አለም ላይ መተኪያ የሌላቸው አንድ አንድ ሰዎች አሉ።ከነሱ ውስጥ አንዱ ሙሉቀን መለሠ ነው ብዬ ለመናገር ቅንጣት አለመነታም። ሰንቶቻችን ከታክሲ መውረጃችንን አልፈን እንደሄድን ያለፍንበት ዘመን ይቁጠረው። ከ30 ዓመታት ባለይ ኑሮውን አሜሪካ ያደረገው ሙሉቀን መለሰ የሙዚቃውን ዓለም በመተው በመንፈሳዊ የሙዝሙር ሥራዎች ውስጥ ያሳልፍ እንደነበር ይታወሳል። ተወዳጁ ሙሉቀን መለሰ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የተቀረፀ የድምፅ ቃለ ምልልስም ሆነ የሙዚቃ ስራ ባይኖረዉም ሙዚቃ መጫወት ከጀመረበተ ከፈጣን ኦኬስትራ 1958 ጀምሮ እስከ1975 ዓ.ም የሰራቸውን በርካታ ተወዳጅ ስራዎቹን አበርክቶልናል:: ገና የ13 ታዳጊ ሳለ ነበር ሙዚቃን የጀመረው። በ1958 ዓ.ም በፈጣን ኦርኬስትራ ውስጥ ተቀላቅሎ በመግባት ለሁለት ዓመታት ያህል ሲያገለግል ከእዚያ በማስከተል በ1960 ዓ.ም ወደ ፖሊስ ኦርኬስትራ ክፍል በመግባት ይበልጥ በሙዚቃ ስራው ዝናን ማትረፍ ችሎም ነበር። በ1972 ዓ.ም ላይ ደግሞ ከዳህላክ ባንድ ጋር ተቀላቅሎ እስከ 1980ዎቹ ድረስ በነበሩት እጅግ ተወዳጅ የሙዚቃ ስራዎችን ሊያደርሰን ችሏል። ከ1980ዎቹ በኋላ ፊቱን ወደ መንፈሳዊ ሥራዎች በማዞር የመዝሙር ሥራዎችን ሲሠራ የቆየ ሲሆን እስከ ህልፈተ ሕይወቱ ድረስ በሀገረ አሜሪካ በእዚያው ቆይቷል። ሙሉቀን ሙዚቃ በቃኝ ብሎ ራሱን ከሙዚቃው ዓለም እስካገለለበት ጊዜ ድረስ በርካታ የሙዚቃ ሥራዎችን የሰራ ታላቅ ኢትዮጵያዊ ጀግና ነው🙌። ሁሌም የሙሌ ሙዚቃዎቹ ከአፍ አይጠፉም "ባሳብ መዋለሌ , ቁመትሽሎጋ ነው ,አይኔማ ወዳጅሽ .....የቱ ተነስቶ የቱ ይተዋል በቆየበት አጭር የሙዚቃ ግዜ ዘመን የማይሽራቸው ስራዎችን አበርክቶልናል። ከዛም ባሻገር ድንቅ ሙዚቀኞችን በስራዎቹ ፈጥሮልናል 🙌🥺 ዛሬ እሱ ቢያልፍም ስራዎችህ ከመቃብር በላይ ህያው ሆነው ከዘመን ዘመን በከፋታ ይኖራሉ ነፍስህ ከደጋጎቹ ዘንድ ትረፍ ነፍስ ይማር🙏🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ሙሉቀንመለሰ #ምነውከረፈደ #musictube369 #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ሙሉቀን መለሰ🥺💔 ''ምነው ከረፈደ'' Sound Effects Free Download. Sound Effects Downloader To Help You Download The Highest Quality ሙሉቀን መለሰ🥺💔 ''ምነው ከረፈደ'' Sound Effects Free Download For TikTok Videos. You Just Search Sound Effects And Download.

My You Like It