"ሳላምንበት"🧡🙌 እንደዛሬ ቀፋይ ሳይበዛ😊በ90ዎቹ ያሉ sound effects free download
By musictube369
920 Downloads
1 weeks ago
277 seconds
About "ሳላምንበት"🧡🙌 --እንደዛሬ ቀፋይ ሳይበዛ😊በ90ዎቹ ያሉ Mp3 Sound Effect
"ሳላምንበት"🧡🙌 --እንደዛሬ ቀፋይ ሳይበዛ😊በ90ዎቹ ያሉ ተፈቃቃሪ ጥንዶች ኑሮን ለማሸነፍ በተለይ ሴቷ ወደ ባህር ማዶ በተለይ አረብ ሃገራት በስደት መጓዟ የተለመደ ነበር። ናፍቆትና ችግራቸውን ተቋቁመው እውነትም እንደ ህልማቸው ኑሯቸውን ያቀኑ ጥንዶች እንዳሉ ሁሉ በወንድ ፍቅረኞቻቸው የተከዱ ሴቶች እንዲሁም ፍቅረኞቻቸው የውሃ ሽታ የሆኑባቸው ወንዶች ሞልተዋል። ኪነ-ጥበብ ዘመኗን ትመስላለች። አፍቃሪዎቹ ከተፈቃሪዎቹ ጋር የተራራቁ በመሆኑ ትዝታና ናፍቆት እንደሚያጋራቸው ቢጠበቅም ገጠመኛቸውና ጥያቄያቸው፤ሙግትና ሃሳባቸው ግን የተለያዩ ናቸው። 🎵ሳላምንበት የመሄዷን ያው ሸኘኋት ይዤ ጓዟን ለኔ ትታው ትዝታዋን ለማስቀረት አቅሙን ያጣሁ ተመለስኩ እያነባሁ ... አዎ ውድ ቤተሰቦቼ ለዛሬ የብዙ ሙዚቃዎች የግጥም ዜማ ደራሲ ድምፃዊ ብስራት ጋረደው በ1997 አ.ም በትሁቱ በዳግማዊ አሊ ፊት አውራሪነት ሀሳቦቹን ፀንሶ በዜማና በግጥም እንዲሁም በማይዘነጋ ቅላፄ ኩልል ባለ ድምፅ አምጦ የወለደውን "ሳላምንበት" አልበምን በ ቁ.30 የሚጣል ዘፈን የሌላቸው አልበሞች ዳሰሳችን ለእናንተ ለትውስታ ይዤላቹ መጥቻለሁ🥰🙏🙌 የብስራት ጋረደው ስም በብዙ ኢትዮጵያውያን ዘንድ ሲነሳ፣ ወደ አእምሮ የሚመጣው የግጥምና ዜማዎቹ ጥልቀትና የቋንቋው ውበት ነው። ለተለያዩ ድምጻውያን ስለሰጣቸው ግጥምና ዜማዎች ትተን "ሳላምንበት" በሚለው ተወዳጅ አልበሙ ስለሚታወቀውና በሙዚቃው ዓለም የራሱን አሻራ ስላሳረፈው ድምጻዊ ትንሽ እናውራ። ታሪኩ የሚጀምረው፣ ድምጻዊው ከደጋፊዎቹ አይን ለተወሰነ ጊዜ ሲሰወር ነው። በስተጀርባ ግን፣ ማንም ያልጠበቀው ከባድ የህይወት ፈተና ገጥሞት ነበር። ብስራት በግልጽ እንደተናገረው፣ በድንገት በ"ስትሮክ" ህመም ተመቶ ለከባድ የጤና እክል ተዳርጎ ነበር። በአንድ ወቅት መድረክ ላይ ቆሞ በሺዎች ፊት ድምጹን ያሰማ የነበረው አርቲስት፣ በቅጽበት በህይወትና በሞት መካከል በሚደረግ ትግል ውስጥ ራሱን አገኘው። ይህ ሁሉ ሲሆን፣ እርሱ ከሙዚቃ ባልደረባው ዳግማዊ አሊ ጋር በመሆን አዲስ አልበም ሰርቶ ለማውጣት ጥግ ላይ ደርሶ ነበር። የዓመታት ልፋቱ ውጤት ሊያይ፣ አድናቂዎቹ አዳዲስ ስራዎቹን ሊሰሙ በጉጉት በሚጠብቁበት ወቅት ነበር ይህ ያልተጠበቀው መከራ የገጠመው። ከከባድ ህመሙ ጋር ሲታገል ከቆየ በኋላ ግን፣ ብስራት እንደሚለው፣ "እግዚአብሔር ፈወሰኝ።" ይህ የፈውስ ተአምር፣ ለህይወቱ አዲስ ትርጉም፣ ለድምጹም አዲስ አላማ ሰጠው። ያ ሊወጣ የነበረው ሙሉ አልበም፣ ያ የዘፈን ዓለም፣ ከዚህ አዲስ የህይወት ምዕራፍ ጋር አብሮ የሚሄድ አልነበረም። ድምጻዊው፣ ከሞት አፋፍ ያተረፈውን አምላኩን ለማመስገን ወሰነ። ውሳኔውም ከባድ ነበር፤ ነገር ግን ለእርሱ ግልጽ ነበር። "ፈጣሪዬ ሌላ የሕይወት ዕድል ስለሰጠኝ፣ ያቆመኝን እርሱን ለማመስገን በዝማሬ እመለሳለሁ እንጂ ወደ ዘፈን ዓለም ተመልሼ አልመጣም" ሲል ብስራት ጋረደው በቁርጠኝነት ተናግሯል። የድምጻዊ ብስራት ጋረደው ታሪክ፣ አንድ ሰው በህይወቱ ከባድ ፈተናን ካለፈ በኋላ እንዴት አዲስ መንገድን ሊመርጥ እንደሚችል የሚያሳይ፣ የተስፋና የእምነት ምስክርነት ሆኗል። ብስሬ ከ"ሳለምንበት" ድንቅ አልበም በተጨማሪ ለታደለ ሮባ "ከፍጥረት የግልሽ" ፣ "ስለ አንቺ አወራለሁ"፤ ለታምራት ደስታ "እኛ ነው ማየት"፣ "ሰው አለሁ"፣"ማሪኝ"፣ ለህብስት ጥሩነህ "በሬ ሲንኳኳ"፣ "ይበለኝ"፤ ለጥበቡ ወርቅዬ "የዘላለሜ ነሽ"፣"ማያዬ"፣"ፍሬም ባናይ"፤ ለሀይማኖት ግርማ "ልርሳክ ይበቃኛል"፤ ለመሰሉ ፋንታሁን "በሰላም ዋለ ልቤ"፤ ለሸዋንዳኝ ሀይሉ "እንኳንም ተፈጠርሽ"፤ ለወንድም ጅራ "አጠርጥሪኝ" ... ውብ ዜማዎች ስለሰጠን እናመሰግናለን 🙏 ፈጣሪ ያሰብከውን ያሳካልህ 💛 ጎበዝ ድምፃዊ + እጅግ ጎበዝ ዜማ ደራሲም በመሆን የኢትዮጵያ ሙዚቃ በተለይ 90'S አይረሳም 🙌 ስለ ዳጊ በሰፊው ለመመለስ ቃል እየገባሁ ለዛሬ አበቃው 🙏🙏 🗣ክብር ለሚገባው ክብር እንሰጣለን🙌🙏 @musictube 🇪🇹 #fyp #ብስራትጋረደው #የ90ዎቹ #ሳላምንበት #musictube369"ሳላምንበት"🧡🙌 እንደዛሬ ቀፋይ ሳይበዛ😊በ90ዎቹ ያሉ Sound Effects Free Download. Sound Effects Downloader To Help You Download The Highest Quality "ሳላምንበት"🧡🙌 እንደዛሬ ቀፋይ ሳይበዛ😊በ90ዎቹ ያሉ Sound Effects Free Download For TikTok Videos. You Just Search Sound Effects And Download.