About አንዳንድ ቀን አለ መሻትህን መግለፅ፣ Mp3 Sound Effect
አንዳንድ ቀን አለ መሻትህን መግለፅ፣ ለምኞትህ፣ ለዓላማህ መልፋት ከንቱ እንደሆነ እንዲሰማህ የሚያደርግ። ማን አለኝ ስትል ልትጥራ የምትችለው ሰው የምታጣበት፣ በጣም ሲከፋ ደግሞ አምላክህ እንዳለህ ለመናገር እንኳ ከርሱ ርቀህ ትዝ እያለህ እንዳልሆነ እንደሆነ የምታውቅበት አንዳንድ ቀን አለ። ምን ላይ ነህ ስትባል ምንም ያሳካኸው ነገር እንደሌለ የሚሰማህ፣ ኤጭ ምናለ እንደው ሰዎች ብዙ ካግበሰበሱ በኋላ አንዲህ ባልሰራሁ ብለው የሚሉትን እንኳ በሰራሁና እንደሰው የምናገረው በኖረ ብለህ የምትመኝበት አንዳንድ ቀን አለ። ድክም፣ ዛል፣ ድብት የምትልበት፣ ውስጣዊ ቁስለቶችህ አቅምህ ላይ እንደ መዥገር ተጣብቀው የብርታት ደምህን እየመጠጡ ፍሬ አልባ እያደረጉህ እንደሆነ ታውቆህ የምትጮህበት የምትተነፍስበት ነፃነት እንደሌለህ ሲገባህ ዝም ጭጭ ብለህ ሁሉንም ጥልት የምታደርግበት አንዳንድ ቀን አለ። ሌላም ብዙ ብዙ…… « አንዳንድ ቀን አለ ስብራቶችሽ ሁሉም ትዝ የሚሉሽ፣ ውል አልባ የሆነ ባዶነት የሚሰማሽ። አልቅሰሽም አይወጣልሽ፣ ጮኸሽም የማይተውሽ አይነት። ጠንካራ ያልሻቸው ሲልፈሰፈሱ፣ መካሪዎችሽ የአደብ ልጓማቸውን በጥሰው በእሾህ ላይ ሲረማመዱ የምታዪበት አንዳንድ ቀን አለ። ዳግም ከመገንባት ያለውን እስከነግሳንግሱ መቀበል የተሻለ ነው ብለሽ የምታስቢበት፣ መትተው አሞሽ፣ መፈለግ ርቦሽ ከንቱ የሆነ ህይወት እየመራሽ እንደሆነ የሚሰማሽ ወቅት አለ። ኤጭ ምነው ይህን ላገኝ ያን ያህል ባልለፋስ፣ እንደማንም ምንም አድርጌ ቢያንስ ከምንም በላይ ለማስቀድማቸው የሆነ ነገር ባደረግኩ ብለሽ ስክር የምትዪበት፣ ሰው ስኬቱን ሲያወራ አንቺ ከስረሻል ከእንግዲህ ምንም ብትለፊ ምንም አታመጪም እያለሽ ያለ እየመሰለሽ ማንንም መስማት የምትጠየፊበት አንዳንድ ቀን አለ። ሁኔታሽ ሁሉ ልክ 9ወር አርግዛ ልጇ በሆዷ ውስጥ እንደሞተባት ሴት አይነት የሚሆንበት። ታድያ የሚገርመው ሙታን እንጂ የማይቀርላቸው ቀብር ውስጥ ያልገቡቱ ላተቅነጡ ሚን ራህመቲላህ(ከአላህ እዝነት ተስፋ አትቁረጡ) የሚለውን አያህ ይመሰክሩ፣ ያረጋግጡ ዘንድ እድል አላቸው። ምድር ለመሸከም የሚከብዳት አይነት ወንጀል ቢሰሩ እንኳ አል ተዋብ ዘንድ የመሄድ ምርጫ ያላቸው እነዝያ ወደ ቀብራቸው የሚገቡቱ እንጂ ከቀብራቸው ውስጥ ያሉት አይደሉም። አጂብ ነው መቼስ የጀሊሉ ስራ… አንዱን ባርያውን መመላለሱን ወዶለት ወደርሱ የሚያመላልሰውን ጉዳይ ይሰጠዋል። ላንዱ ባርያው ደግሞ መሻቱን ፈፅሞለት ሊያመሰግነው ይመጣ ዘንድ ይወድለታል። እርሱ መቼስ ከመስጠቱ ጋር ስስትም የለው፣ ና ባርያዬ ሰፊ እዝነቴን ውሰድ ይላል። እንግዲህ ያወቁቱ እርሱ ዘንድ መመላለስ አለመተዋቸው ከምድራዊ ጸጋዎች ሁሉም በላጩን እንደተሰጡ ይረዳሉ። እንደው ጌታዬ በችግሬ አንተ ዘንድ ተመላልሼ በድሎት ጊዜ አንተ ዘንድ ከመምጣት እንዳልቦዝን ከጠየቅኩህ መሻትና ድሎት አስበልጠህ የወደድክልኝ ስጠኝ ይሉታል። ከሪም መሆኑን ለጥቀው የተረዱቱ ጌታዬ የምጠይቅህን እንደሚበጀኝ እንደምትወድልኝ አድርግልኝ ይላሉ። መቼስ እርሱ ዘንድ ተመላልሶ የከሰረ ማን አለ? (ማንም) አንዳንድ ቀን ግራ ግብት፣ ምስቅልቅል ይል ይሆናል፣ ግና የጊዜያቱ ባለቤት የሆነ ጌታ አለንና ያበረታናል እንደ እርሱ ፍቃድ። ጌታዬ አንተ ዘንድ መመላለሴን ውደድልኝ እንጂ የምሻውም የምናፍቀውም አንተ ዘንድ ከመሰንበት አይበልጥብኝም እንበለው። መቼስ እዝነቱ ረቂቅ ነው፣ ከማወቅም ከመረዳትም አቅም በላይ ነው። ከእዝነቴ ተስፋ አትቁረጡ ብሎ እንዲያዝንለት የጠየቀውን ባርያውን ሳይክስ አይመልሰም። እንግዲህ አላህ ሲክስ እንደ ሰው አይደለም። ላሻው ይመለከተው ዘንድ በጀነቱ መደላደያውን ያመቻችለታል። ላሻው ከቅርቢቱ ዓለም የሻውን ይሰጠዋል። ሩቁን አዋቂ፣ የምስጢራት ባለቤትም አይደል ለሻው ባሻው መልኩ የሻውን ይለግሰዋል። በመስጠቱ፣ በመምረጡ ላይ ከስህተትም ሆነ ከጉድለት የጠራ ከመሆኑ ጋር ያ ደጋግሞ እዝነቱን የጠየቀው ባርያው ከጠበቀው ውጪ ምላሽ ቢሰጥ እንኳ እርሱ ሁሌም ልክ ነው። አላህ አይደል! ባርያው የማያውቀው፣ ያላወቀው፣ ምናልባት ቢያሳውቀው ልቡ ስብር እንዳይል የደበቀው ያልገለጠለት ነገራት ይኖራልና የሻውን ይወስናል። መከፋት፣ ማዘን፣ ድብት ውስጥ መግባት፣ ነገሮች የማይስተካከሉ መመስላቸው፣ መዛላችን፣ ስነ ልቦናችን ጥንብዝ ብሎ እንደሰከረ ሰው መንገዳገዱ ተፈጥሯዊ ነው። መኖራችን በማግኘት እና በስኬት ብቻ የሚለካ አይደለም፣ በዝቅታችን ባልተሳኩ ድካሞቻችንም ላይ ይታያል። ሙታን የሌላቸው እድሎች አሁንም አለንና የምንናፍቀውን ውብ የሰላም ጀንበር የምናይበት ጊዜ ይኖራል። መቼ፣ እንዴት የሚለው የሁሉም ነገራት ባለቤት የሆነው አላህ ያውቃል። ብቻ አብሽሩ! ሰላም ለልባችሁ! » [ አብዱልሀኪም ሰፋ ] #fyp #foryoupage #viral #tiktok #videoአንዳንድ ቀን አለ መሻትህን መግለፅ፣ Sound Effects Free Download. Sound Effects Downloader To Help You Download The Highest Quality አንዳንድ ቀን አለ መሻትህን መግለፅ፣ Sound Effects Free Download For TikTok Videos. You Just Search Sound Effects And Download.