ዓርብ ነሃሴ 24, 1988 ዓ/ም sound effects free download

By cush.n5

0 Downloads

21 hours ago

112 seconds

cush.n5 Sound Effects

About ዓርብ ነሃሴ 24, 1988 ዓ/ም Mp3 Sound Effect

ዓርብ ነሃሴ 24, 1988 ዓ/ም አርቲስት ኤብሳ አዱኛ እና ጓደኛውን ጠና ወይሳ ሽሮ ሜዳ አምሃ ደስታ ት/ቤት አጠገብ ከሚገው መኖሪያ ቤቱ ከእንቅልፍ እንደተነሱ በግፍ ተገድለው አስከሬናቸው ከቤት እየተጎተተ ወጥቶ የመንግስት ታርጋ በለጠፈ መኪና ተጭኖ መወሰዱንና የመንደሩ ነዋሪዎች የድምፃዊ ኤብሳ አስከሬን እየተጎተተ ሲወሰድ ከወገብ በላይ በደም ተለውሶ እንደነበረ የአይን እማኞች የመሰከሩ ሲሆን በግፍ በተገደሉ ሰዓት በነበረው የተኩስ ድምጽ በአቅራቢያ ያለች ወጣት ሴት ደንግጣ በወጣችበት ሰዓት አንች ኦሮሞ ነሽ ? ብለው ሲጠይቋት አይደለሁም ብላ ከሞት እንደተረፈች ኡርጂ በአርቲስቱ የግፍ ግድያ ዜናው ያትታል። ቅዳሜ ማለዳ በማግስቱ የኡርጂ ጋዜጣ ዝግጅት ክፍል የአርቲስት ኤብሳ አዱኛ እና ጓደኛውን ጠና ወይሳ አስከሬን ወደሚገኝበት ምኒልክ ሆስፒታል በመገኘት ከበርካታ አስከሬኖች መካከል የአርቲስት ኤብሳ አስከሬን በደረቱ ወደታች ተደፍቶ ተጋድሞ አግኝቶታል ይላል የኡርጂ ነሃሴ 28, 1988 ዓ/ም የፊት ለፊት እትም ዜናዋ ። ኡርጂ ጋዜጣ ስለ አርቲስት ኤብሳ አዱኛ በፃፈችው ምስክርነት አርቲስት ኤብሳ አዱኛ በህይወት ዘመኑ ሰው አክባሪና አፍቃሪ : ከማንም ጋር የመግባባት ከፍተኛ ችሎታና ተሰጥኦ የነበረው : ለወገኖቹና ሰብአዊና ብሄራዊ መብቶች መከበር ራሱን አሳልፎ የሰጠ ፣ በተሰማራበት የሙዚቃ ሙያ መስክ በሚያደርገው እንቅስቃሴም ትኩረት የሚያደርገው በዚሁ የሰብአዊ መብቶች መከበርና የነፃነት ትግል ላይ መሆኑን ከቅርበት የሚያውቁት ጓደኞቹና የስራ ባልደረቦቹ ይናገራሉ ። አርቲስት ኤብሳ አዱኛ የትውልድ አካባቢው ወለጋ , ደምቢዶሎ ቢሆንም ያደገውና አብዛኛው የወጣትነት የህይዎት ዘመኑን በቦረና ነበር ። የአርቲስት ኤብሳ አዱኛ አስከሬን እሁድ ነሃሴ 26,1988 ዓ/ም ወላጆቹ ወደሚገኙበት ደምቢ ዶሎ መሄዱን ኡርጅ እንዲህ ዘግባለች። ስም ከመቃብር በላይ ነው አርቲስት ኤብሳ አዱኛ ለኦሮሞ ህዝብ ፍትህ : እኩልነት : ነፃነት ለከፈለው የህይወት መስዋዕትነት እና ለኦሮሞ የኪነጥበብ እድገት ለአበረከተው ልዩ አስተዋጽኦ ሁሌም በትውልድና በታሪክ ህያው ነው !#ethiopian_tik_tok #oromotiktok❤️💚❤️ #ethiopia #oromotiktok #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹
ዓርብ ነሃሴ 24, 1988 ዓ/ም Sound Effects Free Download. Sound Effects Downloader To Help You Download The Highest Quality ዓርብ ነሃሴ 24, 1988 ዓ/ም Sound Effects Free Download For TikTok Videos. You Just Search Sound Effects And Download.

My You Like It

Upload By CUSH NATION.5 MEDIA✔️